BEGIN:VCALENDAR
VERSION:2.0
PRODID:-//Meqoamia - ECPv5.12.1//NONSGML v1.0//EN
CALSCALE:GREGORIAN
METHOD:PUBLISH
X-WR-CALNAME:Meqoamia
X-ORIGINAL-URL:https://meqoamia.org
X-WR-CALDESC:Events for Meqoamia
REFRESH-INTERVAL;VALUE=DURATION:PT1H
X-Robots-Tag:noindex
X-PUBLISHED-TTL:PT1H
BEGIN:VTIMEZONE
TZID:UTC
BEGIN:STANDARD
TZOFFSETFROM:+0000
TZOFFSETTO:+0000
TZNAME:UTC
DTSTART:20210101T000000
END:STANDARD
END:VTIMEZONE
BEGIN:VEVENT
DTSTART;VALUE=DATE:20210720
DTEND;VALUE=DATE:20210721
DTSTAMP:20260509T190355
CREATED:20211119T124214Z
LAST-MODIFIED:20211119T132007Z
UID:3214-1626739200-1626825599@meqoamia.org
SUMMARY:Joint Inspection & Site Vist at 3 woredas of Arada Sub-City
DESCRIPTION:የምክትል ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ፣የፍትህ አካላት፣ የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮች እና አጋር አካላት በትናንትናው እለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ትንባሆና አደንዛዥ እጽ ላይ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦችን በአካል ወርደው አረጋገጡ፡፡ \n************************ \nአዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ነጻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦቸን ከከንቲባ፣ ከፌደራል ምግብ መዳህኒት፣ከፍትህ አካላት፣የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮችና አጋር አካላት በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጤናና የምግብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በትንንትናው እለት ማለትም ሀምሌ 12/2013 ዓ.ም በአካል ወርደው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ገመገሙ፡፡ \nከታዩት ተቋማት ውስጥ ጥቂቶቹ ዘርፉን ከሚመሩት ባለሙያዎች ተከታታይ የሆነ ግንዛቤ፣ክትትልና ድጋፍ ስለተደረገልን የትንባሆን የጤና ጎጅነትና አስከፊነት ግልጽ ግንዛቤ ይዘን ተቋማችን ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ችለናል ሁኖም ግን ለመከላከል ስንጀምር ደንበኞች ቢያስቸግሩንም እየቆየን በማግባባትና ግንዛቤ በመፍጠር ያለውን የጤና ጉዳት በማስረዳት ከ10 ሜትር አልፈን ግቢያችን ነጻ ለማድረግ ችለናል፣ከዚህ በተጨማሪ ለስራችን እንዲያግዘን ለፖሊስና ለፍትህ አካላት ግንዛቤው በስፋት ቢሰጥ እና ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ የማያዳግም እርጃ ቢወሰድ ለውጡን ለማስቀጠል እንበረታለን ሲሉ የቀስተ ደመና ሆቴል ሰራተኛና ተወካይ የሆኑት አቶ ሞላልኝ አየነው ገልጸዋል፡፡ \nበተጨማሪም የኤልቤት ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አያሌው ዘለቀ ይህ ቦታ የሀሺሽ፣የሺሻ፣የሲጋራ የጫትና የአልኮል መጠቀሚያ የትውልድ መግደያ ቤት ነበር አሁን ግን ከዘርፉ ባገኘነው ስልጠና ት/ትና ግንዛቤ ወስደን ሲጋራና ትንባሆ ምንም ጥቅም የሌለው ከአጫሹ ይልቅ ተቀማጩን የሚጎዳ ለጤናችንም ለስራችንም አጸያፊ መሆኑን ተገንዝበን ጥቅማችን ትተን የሺሻ መደበቂያ የነበረውን ፑል አቁመን ግቢያችን ውስጥ ምንም አይነት ትንባሆና አደንዛዥ እጽ እንዳይጠቀሙ የሚያስጠነቅቅ ባነር በመለጠፍ ተቋማችን ሙሉ ለሙሉ ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ችለናል።\nእንደዚህ በማድረጋችን እጅግ ደስተኞች ነን በማለት አስተያየታቸውን ጭምር ገልጸዋል፡፡ \nየምክትል ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፓውሎስ ኩሳ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማ ደረጃ እየተሰራ ያለው የስራ ጅምርና ጥረት በጣም ሊበረታታ የሚገባ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ የሚያስችል ጥረት እንደሆነ ገልጸው ባየናቸው ተቋማት በሚሰጡት መልስ ግንዛቤ እንዳላቸው ላማረጋገጥ ችያለሁ ከታዩት ውስጥም ሲጋራ ሲጨስ አላየንም ይህም አንዱ ለውጥ ነው በማለት ባዩት ጅምር ስራ ደስታቸውን ገልጸው ይህ ጥረት እንዳይቆምና ቀጣይነት ኑሮት ሲጋራን ተጸያፊ ትውልድል ለመፍጠር ኅብረተሰቡ፣የፍትህ አካላት እና ተቆጣጣሪ አካሉ በቅንጅት መስራት አለባቸው ስራው በምሽትም ተጠናክሮ መቀጠልና ለውጡን በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ ይገባል በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ \nየባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ በተቋማት ላይ ሲጋራንና ትንባሆን ማስጨስ ጤናን ከመጉዳቱ ባሻገር በህግ የተቀመጠ ወንጀል ነው ስለዚህ በተሰጣችሁ ግንዛቤ፣በሚደረግላችሁ ክትትልና ድጋፍ ተቋማችሁን መለወጥና ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ካልቻላችሁ ወንጀልን የመከላከል ስራ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አውቃችሁ የተጀመረውን ነገር በማታም በቀንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው ለስራችሁ መሳካት የከንተማው ከንቲባ፣የፍትህ አካላትና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከጎናቸው ሁኖ እንደሚደግፋቸው ለተጎበኙት ተ ቋማት ባለቤቶችና ተወካዮች ጠንከር ያለ መልክት አስተላልፈዋል።
URL:https://meqoamia.org/event/joint-inspection-site-vist-at-3-woredas-of-arada-sub-city/
ATTACH;FMTTYPE=image/jpeg:https://meqoamia.org/wp-content/uploads/2021/11/photo_2021-11-19_16-08-39.jpg
END:VEVENT
END:VCALENDAR