Loading Events

« All Events

  • This event has passed.

Joint Inspection & Site Vist at 3 woredas of Arada Sub-City

July 20, 2021

inspection

የምክትል ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ፣የፍትህ አካላት፣ የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮች እና አጋር አካላት በትናንትናው እለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ትንባሆና አደንዛዥ እጽ ላይ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦችን በአካል ወርደው አረጋገጡ፡፡

************************

አዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ነጻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦቸን ከከንቲባ፣ ከፌደራል ምግብ መዳህኒት፣ከፍትህ አካላት፣የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮችና አጋር አካላት በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጤናና የምግብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በትንንትናው እለት ማለትም ሀምሌ 12/2013 ዓ.ም በአካል ወርደው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ገመገሙ፡፡

ከታዩት ተቋማት ውስጥ ጥቂቶቹ ዘርፉን ከሚመሩት ባለሙያዎች ተከታታይ የሆነ ግንዛቤ፣ክትትልና ድጋፍ ስለተደረገልን የትንባሆን የጤና ጎጅነትና አስከፊነት ግልጽ ግንዛቤ ይዘን ተቋማችን ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ችለናል ሁኖም ግን ለመከላከል ስንጀምር ደንበኞች ቢያስቸግሩንም እየቆየን በማግባባትና ግንዛቤ በመፍጠር ያለውን የጤና ጉዳት በማስረዳት ከ10 ሜትር አልፈን ግቢያችን ነጻ ለማድረግ ችለናል፣ከዚህ በተጨማሪ ለስራችን እንዲያግዘን ለፖሊስና ለፍትህ አካላት ግንዛቤው በስፋት ቢሰጥ እና ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ የማያዳግም እርጃ ቢወሰድ ለውጡን ለማስቀጠል እንበረታለን ሲሉ የቀስተ ደመና ሆቴል ሰራተኛና ተወካይ የሆኑት አቶ ሞላልኝ አየነው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የኤልቤት ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አያሌው ዘለቀ ይህ ቦታ የሀሺሽ፣የሺሻ፣የሲጋራ የጫትና የአልኮል መጠቀሚያ የትውልድ መግደያ ቤት ነበር አሁን ግን ከዘርፉ ባገኘነው ስልጠና ት/ትና ግንዛቤ ወስደን ሲጋራና ትንባሆ ምንም ጥቅም የሌለው ከአጫሹ ይልቅ ተቀማጩን የሚጎዳ ለጤናችንም ለስራችንም አጸያፊ መሆኑን ተገንዝበን ጥቅማችን ትተን የሺሻ መደበቂያ የነበረውን ፑል አቁመን ግቢያችን ውስጥ ምንም አይነት ትንባሆና አደንዛዥ እጽ እንዳይጠቀሙ የሚያስጠነቅቅ ባነር በመለጠፍ ተቋማችን ሙሉ ለሙሉ ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ችለናል።
እንደዚህ በማድረጋችን እጅግ ደስተኞች ነን በማለት አስተያየታቸውን ጭምር ገልጸዋል፡፡

የምክትል ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፓውሎስ ኩሳ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማ ደረጃ እየተሰራ ያለው የስራ ጅምርና ጥረት በጣም ሊበረታታ የሚገባ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ የሚያስችል ጥረት እንደሆነ ገልጸው ባየናቸው ተቋማት በሚሰጡት መልስ ግንዛቤ እንዳላቸው ላማረጋገጥ ችያለሁ ከታዩት ውስጥም ሲጋራ ሲጨስ አላየንም ይህም አንዱ ለውጥ ነው በማለት ባዩት ጅምር ስራ ደስታቸውን ገልጸው ይህ ጥረት እንዳይቆምና ቀጣይነት ኑሮት ሲጋራን ተጸያፊ ትውልድል ለመፍጠር ኅብረተሰቡ፣የፍትህ አካላት እና ተቆጣጣሪ አካሉ በቅንጅት መስራት አለባቸው ስራው በምሽትም ተጠናክሮ መቀጠልና ለውጡን በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ ይገባል በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ በተቋማት ላይ ሲጋራንና ትንባሆን ማስጨስ ጤናን ከመጉዳቱ ባሻገር በህግ የተቀመጠ ወንጀል ነው ስለዚህ በተሰጣችሁ ግንዛቤ፣በሚደረግላችሁ ክትትልና ድጋፍ ተቋማችሁን መለወጥና ከሲጋራ ጭስ ነጻ ማድረግ ካልቻላችሁ ወንጀልን የመከላከል ስራ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አውቃችሁ የተጀመረውን ነገር በማታም በቀንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው ለስራችሁ መሳካት የከንተማው ከንቲባ፣የፍትህ አካላትና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከጎናቸው ሁኖ እንደሚደግፋቸው ለተጎበኙት ተ ቋማት ባለቤቶችና ተወካዮች ጠንከር ያለ መልክት አስተላልፈዋል።

Inspection

Details

Date:
July 20, 2021

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies