መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት በ የቀድሞ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ‹ፓን አፍሪካኒስት› ባለ ራዕይ ተማሪዎች ተነሳሽነት የአደንዛዥ – እፆች ተጠቃሚነትና ሱሰኝነትን እንዲሁም አደንዛዥ አስተሳሰብን ለመከላከል በ2003 ዓ.ም የተመሰረተ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱ በ ህዳር 22, 2002 በበጎ አድራጎቶች መደራጃ አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 621/2009 መሰረት ፍቃድ አግኝቶ ስራ የጀመረና በመዝገብ ቁጥር 2099 ፣ የሚታወቅ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ነው፡፡ህግን የሚጠብቅ ፤ ሪፖርት እና እቅድ በወቅቱ የሚያሳውቅ ፤ በጊዜው እድሳት የሚያደርግ ድርጅት ነው፡፡
180 የጠቅላላ ጉባኤ እና 5 የቦርድ አባላት ሲኖሩት ኦዲተር ፣ ስራ አስኪያጅ ፣ የዕቅድና ክትትል የህዝብ ግንኙነት፣ሃብት አፈላላጊ ፣ የአስተዳደርና ፋይናስ ፣ የፕሮግራም አስተዳዳሪ ፣ የቅድመ መከላከል ፣ የጥናትና ምርምር ፣ ሂሳብ ሹም የህክምና እና ማገገሚያ የስራ ክፍሎችን ያካተተ ድርጅት ነው::