- This event has passed.
University Based Anti Addiction Community Movement /UBAACM/ – No tobacco day May 31,2019
December 31, 2019
University Based Anti Addiction Community Movement /UBAACM/
“ዩኒርስቲዎችን መሰረት ያደረገ የፀረ አደገኛ እፆች ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ ”
No tobacco day May 31,2019
አለም አቀፍ የትንባሆ የማይጨስበት ቀን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ መድረክ።
ምስጋና
ይሄ ትውልድ በአገሩ ኢትዮጵያ በመጭው ትውልድ የሚታወስበትን አሻራ አስቀመጠ!! ሃውልት አቆመ!
የምግብ መድሃኔት ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 መውጣት ከጠቅላላ ህዝባችን 71% ከ30 አመት በታች 41% ደግሞ ከ15አመት በታች በሆነባት አገር በአንድም በሌላ መንገድም ባለ አዲስ ነገሮችን ለማወቅ በሚነሳሳ የታዳጊ ወጣቶች ፍላጎት በቢራ ማስታወቂያዎች ገደብ ያጣ ሳቢና አጓጊ ማራኪ ማስታወቂያዎች ተነሳስተው ምን ያህሎች መጠጣት እንደ ጀመሩና እንደሚጀምሩ በየአካባቢያችን ያለውን ጫና መገመት አይከብደንም።
ስለሆነም የትንባሆ አጠቃቀምም ገደብና ቁጥጥር ባለመኖሩ ምክንያት የብዙሃኑ መብት ከመጣስ ባለፋ የሁለተኛ ደረጃ የትንባሆ ጢስ ተጠቂ ብዙዎቻችን ሁነን ቆይተናል።
በመሆኑም በትንባሆ ተጠቃሚዎች ተጠቃሚነት መብታችን ተጥሶ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ተጠቂዎች መብታችንን የሚያስከብረው አዋጅ 1112 ድንጋጌ መውጣት እንደ መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ደስታችን ላቅ ያለ ነው።
ስለዚህ ይህ ትውልድ የሰራው የጀግንነት ተግባር ነው ብለን እናምናለን።
በዋናነት ትንባሆ የሚጎዳው በጭሱ የተጠቁትን ሁሉ ዋና የሰውነት ክፍል የሆነውን አንጎላችንን ጭምር መሆኑ ግልፅ ሆኖ ሊሰመርበት ይገባል።
ይህ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር )1112 እንዲወጣ ጥረት ላደረጉ ፣ለተጉ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ መንግስትን የወተወቱ ፤ እውቀታቸውን ላበረከቱ ፣ ገንበባቸብን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ጊዜቸውን ላበረከቱ ሁሉ የዚህ ዘመን ታሪክ ሰሪዎች ጀግኖች ፤ የሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ሁሉ እንዲሁም ግለሰቦች ሊመሰገኑ ይገባል።
በፎቶው ከሚታዩት በስተጀርባ ብዙ ታሪክ ሰሪዎች አሉ።
ለምሳሌ መቋሚያን ወክሎ ከቆመው ኤልያስ በስተጀርባ በምንም መለኪያ ወደር የማይገኝለት ብዙ ዋጋ የከፈሉ ወጣቶች የመቋሚያ ልጆች እንዳሉ ሁሉ ማለት ነው። ሁሉንም የተወከሉ አካላትን መነሻ አድርገን ከልብ የመነጨ የትውልድ ምስጋና ልናቀርብ እንወዳለን።
እናመሰግናለን!!!!
እናንተ ትውልዱን ወክላችሁ ታሪክ የሰራችሁ ጀግኖች ናችሁ!!!
ከዚህ ቡሃላም ሃይላችሁ ታድሶ አንድነታችሁ ጠኖክሮ በቅድመ ሚከላከል ስራው ላይ አመርቂ ነገር ትሰራላችሁ ብለን እጠብቃለን።
ከፍተኛ ምስጋና ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማናጅመንት እና ለአንቲ ድራግና አልኮል ክለብ ።
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ
ሃገር ማለት ሰው ነው። ሰውን የሚጠብቅ ህግ ሁሉ መላውን ተፈጥሮ የሚጠብቅ ህግ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአለም አቀፍ “ትንባሆ የማይጨስበት ቀን” የግንቦት 24/2011 ዓ.ም በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ የማስታወሻ ፎቶ