Loading Events

« All Events

  • This event has passed.

We are blessed ‘ MCDO’s Grateful Day! ‘

April 8, 2022

[Forwarded from Meqoamia]
#የመቋሚያ_የማህበረሰብ_ልማት_ድርጅት_የምስጋና_ቀን!

መጋቤት 30/2014 ዓ.ም

እነሆ ዛሬ #የምስጋና ቀናችን ነው!

#ለምስጋና #ደስ እያለን ፤ #ስለተደረገልን ነገሮች ፣ #በእኛ በኩል ለማህበረሰባችን ስለተከናወኑት ክንውኖች እና ምርጥ ስኬቶቻችን ለማሰብ…. እንዲሁም
#በማስተዋል ለሚገባው ሁሉ- እውቅና ለመስጠት ፤ በምስጋና መንፈስ በመሆን ለመሰባሰብ….. ፍቃደኛም ስለሆንን – እናንተን እና እድሉን የሰጠን አምላክ ክብርና ምስጋና ይድረስው እላለሁ!!!

የመጭው ዘመን ግማሽ ድል፥ ያለፈውን ዘመን ጉዞ በምስጋና ዘግቶ ፥ ከበረው ልምድም ተምሮ ፣ የጎደለውን ነገር ለመሙላት ተዘጋጅቶ … የመጭውን ዘመን በእምነትና ተስፋ ፥ በድል መንፈስ (ፈጣሪን በመፍራት መንፈስ) የመሞላትና በራዕይ ሃይልና ጉልበት ፥ አጥርቶ በማየት ጉዞ መጀመር መቻል ነው!

የድል ጉዞ ሌላኛው አምድ:- የግለሰቦች አመስጋኝ መሆን መቻል ፥ ይመስለኛል ። ለራሳቸው ከሚኖራቸው ክብርና ለእውነት የሚኖራቸው ወገንተኝነት ፣ የአላማ ታማኝነት እንዲሁም በተሰማሩበት ሃላፊነትና የሙያ ዘርፍ በብቃትና በጥራት ስራን የማከናወን አቅም ፤ በቡድን ስራ ውስጥ ለሚኖር ስኬት ሚናው ትልቅ መሆኑን ተምሬለሁ!

ሌላኛው የቡድን መንፈስ ጥንካሬ እና ጉልበት ትሁታን የቡድን አባላት መኖራቸው መሆኑንም ሌላኛው ትምህርቴ ነው።

ትሁታን ደግሞ አሪፍ አመስጋኝ ናቸው።

በተጨማሪም

የቡድን ስራ ስኬታማነት ፦

ራዕይ ፣ አላማ እና ግብን በግልፅ መረዳት መቻል ፥ ከላይ ከገለፅነው ስብዕና ጋር ሲደመር ለፈጠራ ስራ እንዲሁም አንድኛችን ሌላኛችንን በመደገፍና በመረዳዳት ( መቋሚያ በመሆን ) ለጋራ ውጤታችን እንድንሰራ የሚያደርገ መንገድ ነው።

በዚህ ሁሉ ሰው በእውነተኛ ጉዞ ውስጥ ምስጋናን የሚያቀርብበት የህይወት ስርአት አለው ማለት ፥ ይሄ ሰው የተሳካለት ነው! ለማለት እወዳለሁ!

መቋሚያም በእውነት የማህበረሰቡ ድጋፍ ለመሆን የሚያስችላትን ጉልበት ለማግኘት በአመስጋኝነት መንፈስ ውስጥ መሆኖን ወድጀዋለሁ!

ምስጋና

#ለፈጣሪ
#ለማህበረሰባችን
#ለመንግስታችን
#አብራችሁን ለመስራት ፍቃደኛ ለሆናችሁ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፤ የተከበረው የፖርላማ አባላት እና ሚኒስተሮች
#ሚዲያዎችና_ጋዜጠኞች
#አብረውን_ለሚሰሩ የአገር ውስጥ እና የውጭ አጋሮቻችን
#ለትልቁ የመቋሚያ ቤተሰብ
#ለቦርድ አባሎቻችን
#ለእያንዳንዱ ሰራተኞቻችን
#በአለፋት አመታት በመቋሚያ ውስጥ አገልግሎት ለሰጣችሁ
#በመቋሚያ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ላለፋችሁ ሁሉ
#በተለያየ መንገድ ስታግዙን ለቆያችሁ የመቋሚያ ወዳጆች
#ወዘተ….

ከእናንተ ጋር አብሮ መስራት መታደል ነው!

በመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ስም አክብሮትና ምስጋናየ ይድረሳችሁ!

ኤልያስ

Details

Date:
April 8, 2022

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies