አብይ ዘለቀ / ስነ መለኮት / ከመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ቤተሰብ

“ለ8አመት የአልኮል መጠጥ፣የጫት፣የሲጋራ እና የማሪዋና  ተጠቃሚና  ሱሰኛ እንዲሁም የአደንዛዥ አስተሳሰቦች ሰለባ  ነበርኩ  ፡፡  እነኝህን እፆች መጠቀም የጀመርኩትም  ከ16  አመቴ ጀምሮ ነበር ፡፡ በሱሰኝነት ሕይወቴ  ለብዙ  ጊዜ ትምህርቴን እንዳቋርጥ እና ከቤተሰቦቸ ጋር እንድጋጭ  ምክንያት ሆኖኝ ነበር፡፡በእዚህም በባለፈው  ዘመኔ አላማና እቅድ አልባ ኑሮን እመራ የነበር፡፡ መኖር  ለእኔ ትርጉም ያልነበረውና ለህይወት ግድ የሌለው  ሰው ነበርኩ ማለት ይቻላል፡  

ወደ መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅ ማገገሚያ ማእከል ከገባሁ  እና የማገገሚያ ማዕከሉ  ተጠቃሚ  በመሆኔ  በውስጤ የተቀጣጠለው የለውጥ መነሳሳት እና ቁርጠኝነት ሕይወቴን በተሻለ መንገድ እንድመራ የሚያስችል  ሆነ፡፡ ምክንያቱም ሲደረግልኘ የነበረው የአቻ ድጋፍና አመለካከቴን የሚቀይሩ የማገገም አጋዥ ስልጠናዎች ፤ ከእፆቹ ተጠቃሚነት እንድላቀቅ ብቻ ሳይሆን ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖረኝ የሚያድረጉኝ ሆነውኛል፡፡የአደንዛዥ አስተሳሰብ ተጠቂ  የነበርሁ መሆኔ የገባኝ ያኔ ስለነበር በአስተሳሰቤ ላይ በብርቱ እንድሰራበት እና እንድለወጥ አግዘውኛል፡፡በለውጤ ምክንያት ከእኔ አልፎ  ቤተሰቦቼ እጅግ ደስተኛ በመሆናቸው ለእኔ ልዩ ስሜት የፈጠረልኝ ነገር ነው፡፡

ስለሆነም በመቋሚያ ውስጥ በአገኘሁት የአቻ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የስልጠና ፕሮግራሞች በመጠቀሜ በጽናት መቆም ችያለሁ፡፡ እስከዛሬ ላለፉት 11 አመታትን የእረፍትና ትርጉም ያለው ኑሮን እየኖርኩ አለሁ፡፡

የመቋሚያ  ቤተሰብ እና የአቻ ድጋፉ   ተጠቃሚ  በመሆኔ ክብር ይሰማኛል፡፡ዛሬ በየሄድኩበት ቦታ   “ ከሱስ መውጣት እደሚቻል እና የምንከላከለው  የአአምሮ  ህመም ስለመሆኑ  ምስክርነቴን እሰጣለሁ!!

አብይ ዘለቀ

/ ስነ መለኮት /ከመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ቤተሰብ

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies