ኤልያስ ካልአዩ /የሱስ ህክምና ባለሙያ ፣ የህዝብ አስተዳደር እና የማህበረሰብ እድገት አጥኝ/ የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ኤክስኪውቲቭ ዳሬክተር
”በአስራ ሁለት አመቴ አካባቢ ነው የጀመርኩት ፡፡ በተከታታይ ለአስራ ሶስት አመታት ሲጋራ ፣ማሪዋና ፣ጫት እና አልኮል መጠጥ ተጠቃሚና ሱሰኛ ነበርኩ ፡፡ በእዚህም ምክንያት ለተለያየዩ ስነልናዊ ፣አካላዊ ፣ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና መንፈሳዊ ችግሮች ተጋልጭ ነበር ፤ ራሴንም ቤተሰቤንም ጎድቻለሁ! ሆኖም ግን የመጪውን ዘመኔን አሻግሬ ሳየው በዚሁ መልኩ ከቀጠልኩ ከእኔ አልፎ በቤተሰቤ ላይ ሊፈጠር የሚችለው አደጋ እንደሚከፋ በጥቂቱ ስለ ተረዳኝ ለውጥን ፈለኩ፡፡
ከጥቂት አስቸጋሪ ወቅቶች ቡሃላ በቆራጥነትና በጽናት የለውጥ ተነሳሽነት ራሴን ከእፆች ተጠቃሚነት እና ለመጠቀም ግፊት ከሚያደርጉብኝ የአጠቃላይ ሕይወቴ መረበሽ ምክንያት ከነበሩት የአደንዛዥ አስተሳሰቦች በሂደት በማላቀቅ እረፍት ያለው ነጻ ሕይወትን ልመራ ችያለሁ፡፡
በዚህም እንደ አዲስ የተወለድኩ ያህል ይሰማኛ፡፡
ዛሬ ከእፆች ተጠቃሚነት ነጻ የሆኑ 14 ውብ አመታትን አሳልፊለሁ፡፡ የእኔ አይነት ተመሳሳይ ችግሮች ያለባቸውን አቻዎችን ለመርዳት ራዕይ ሰንቄ በጠቀስኩት ከእጽ ነጻ የሆንኩባቸው አመታትን የምልሰተ ሱስ/ግርሻት ቅድመ መከላከል ፤ የአቻ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያ እና የሱስ ህክምና ባለሙያ አሰልጣኝ /Recovery Coach / በመሆን አለም አቀፍ ስልጠናና ትምህረቶችን በመውሰድ እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡ በርካቶችን በማገዜና አገሬን መርዳት በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል፡፤
በአቻ ድጋፍና ልዩ ልዩ ስልጠናዎችበመስጠቴና በመውሰዴ የተሻለ ለውጥን እንዳመጣ የሚያስችሉ ጥሩ ልምዶችን እዳገኝ አስተዎፅኦ አድርገውልኛል ፡፡
ከሱስ መውጣት እና ሌሎችንም መርዳት እንደሚቻል እኔ ማሳያ ነኝ!
በከፋ ምልሰተ ሱስ እንዳልጠቃ እና በፅናት መኖር እድችል ያስቻለኝም እኔን መሰል ወገኖቸን ለመርዳት ራዕይ መሰነቄ እና ለራዕዩ አላማ የተመቸሁና ለሌሎች የምጠቅም ሰው ለመሆን የሕይወት ስርአቴን መለወጥ በመቻሌ እና እለት እለት የድጋፍ ክትትል በመኖሪ ነው እላለሁ
፡፡ የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት መስራች አካል በመሆኔና ድርጅቱ ውስጥ ማገልገል በመቻሌ ክብር ይሰማኛል፡፡ ”
ከሱስ መውጣት ይቻላል!
ኤልያስ ካልአዩ
/የሱስ ህክምና ባለሙያ ፣ የህዝብ አስተዳደር እና የማህበረሰብ እድገት አጥኝ/
የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ኤክስኪውቲቭ ዳሬክተር