World Drug Day
ሰኔ 26 /2023 የዓለም የአደገኛ እፅ ቀን ነው።
መከላከልን ከርኅራኄ ጋር፡፡
“ሱሰኝነት የምንከላለውና ማገገም የሚችል የአንጎል ህመም ነው!”
ሃገር ማለት ሰው ነው!
የዘንድሮው World Drug Day Jun 6th 2023 ዘመቻ መሪ ቃል፡-
#ቅድሚያ ለሰው! ፡- አድሎ እና መገለል ይቁም ! ፣ ቅድመ መከላከልን ማጠናከር – የአደገኛ ዕፅ ተጠቃሚና ሱሰኞችን በአክብሮት እና እክብካቤ ማከም ፣ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ለሁሉም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ፣ የቅጣትና ማስተማሪያ አማራጮችን መጠቀም ፣ መከላከልን ማስቀደም እና ግንዛቤን ማሳደግ ላይ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከርኅራኄ ጋር፡፡
የዓለም የአደገኛ ዕፅ ችግር በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አደጋ ላይ የጣለ ውስብስብ ጉዳይ ነው ። አደገኛ መድኃኒቶችንና ዕፆችን የሚወስዱ ሰዎች አካላዊና አእምሯዊ ጤንነታቸው አደጋ ላይ ከመውደቅ በተጨማሪ የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዳያገኙ እንኳ ያሉበት ችግር ሊያግዳቸው ይችላል ።
በዚህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደገኛ መድኃኒቶችና ወንጀሎች ቢሮ (UNODC) – በሰብአዊ መብት ፣ ርህራሄ እና በማስረጃ ላይ በተመሰረተ ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ የአደንዛዥ ዕፅ ፖሊሲዎችን በህዝብ ላይ ያተኮረ አቀራረብ የመከተልን አስፈላጊነት ተገንዝቧል።
“ጥላታችን የሱስ ህመሙ እንጅ ሱሰኛው አይደለም !”
መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
ሰኔ 17 /2015 – 24 June 2023