አዲስ አበባ ኢትዮጵያ – MCDO

📌የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት (MCDO) ለዓለም የትንባሆ የማይጨስበት ቀን (WNTD-2026) ባዘጋጀው ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር፣ የትንባሆ ኢንዱስትሪው ወጣቶችንና ህፃናትን ኢላማ ያደረገባቸውን ሶስት ዋና ዋና ስልቶች ያጋልጣል።

⚠️ ተጠንቀቁ! እነዚህ የኢንዱስትሪው ስውር ወጥመዶች ናቸው፦
ዲጂታል ቅስቀሳ (Social Media Targeting)፦ በሶሻል ሚዲያ አማካኝነት ማራኪ በሚመስሉ ምስሎች ወጣቶችን ወደ ሱሰኝነት መሳብ።

የተቀመሙ ትምባሆዎች (Flavored Tobaccos)፦ ህፃናትን ለመሳብ የተለያዩ ጣፋጭ ሽታና ጣዕም ያላቸውን ኬሚካሎች በመጠቀም የሚዘጋጁ መርዞች።

ኢ-ሲጋራ እና ቪፒንግ (E-cigarettes & Vaping)፦ “ጉዳት የለውም” በሚል የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አዲስ የሱሰኝነት መሣሪያ ለትውልዱ ማቅረብ።

💡 ለምን እንከላከላለን?
የእነዚህ ምርቶች ዋነኛ ሰለባ “የአእምሮ ካፒታላችን” ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኒኮቲን የታዳጊዎችን አንጎል እድገት ከመግታት ባለፈ ለአንጎል ስትሮክ እና ለሳምባ ካንሰር ቀጥተኛ መንስኤ ነው።

📢 ጥሪያችን፦
“ካፒታላችንን እንጠብቅ!” የትንባሆ ኢንዱስትሪ ማታለያዎችን በጋራ እንቃወም። ቪፒንግም ሆነ ሲጋራ ለአእምሮ ጤና ጠንቅ ናቸው።

አእምሮን መጠበቅ – ትውልድን መታደግ ነው!

MCDO #WorldNoTobaccoDay2026 #NoVaping #ProtectTheCapital #HealthyBrain #AAFDA #EFDA #Ethiopia #SmokeFreeAddis

ለተጨማሪ መረጃ፦ www.meqoamia.org
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ሀናን ኬ ፕላዛ፣ አዲስ አበባ።

Leave a comment