In Addis Ababa, the tobacco control measures continue to be strengthened: Mayor’s Office. Uncategorized በአዲስ አበባ ከተማ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል፦ የከንቲባ ጽ/ቤትበአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ባለው ሕግ የማስከበር ሥራ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ።በትናንትናው ዕለት በመዲናዋ ከምሽቱ 4:00 እስከ ሌሊቱ 8:30 በከተማዋ የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በአዋኪ ድርጊት ላይ የተደራጀ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።በዚህም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፦ሪቮ አዲስ ላወንጅ፦ 87 የሺሻ ዕቃና በድርጊቱ ተሳታፊ 200 ወጣትአቤም ሆቴል፦ 22 የሺሻ ዕቃና 8 ወጣቶችናሽናል ሆቴል፦ 16 የሺሻ ዕቃ እና 67 ወጣቶችሞሲሳ ሆቴል፦ 7 የሺሻ ዕቃዎችበቦሌ ክፍለ ከተማ5.ቀነኒሳ ሆቴል፦ 35 የሺሻ ዕቃዎች6.ዘባንክ ላውንጅ፦ 28 የሺሻ ዕቃዎችየካ ክፍለ ከተማቤልቪው ሆቴል፦ 86 የሺሻ ዕቃ እና 54 ሰውበአጠቃላይ በሦስት ክፍለ ከተማ 7 ቤቶች ታሽገዋል፤ 281 የሺሻ ዕቃዎች እና 330 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ 200 ወጣቶች በምክር እንዲለቀቁ ተደርጓል።130 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው በሕግ መታየት መጀመሩን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።በተከናወነው ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሰላም እና ፀጥታ፣ የደንብ ማስከበር እንደተሳተፉበት ተገልጿል።EBC Uncategorized January 20, 2023 0Comments Share: