In Addis Ababa, the tobacco control measures continue to be strengthened: Mayor’s Office.

በአዲስ አበባ ከተማ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል፦ የከንቲባ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ባለው ሕግ የማስከበር ሥራ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በትናንትናው ዕለት በመዲናዋ ከምሽቱ 4:00 እስከ ሌሊቱ 8:30 በከተማዋ የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በአዋኪ ድርጊት ላይ የተደራጀ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።
በዚህም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፦
ሪቮ አዲስ ላወንጅ፦ 87 የሺሻ ዕቃና በድርጊቱ ተሳታፊ 200 ወጣት
አቤም ሆቴል፦ 22 የሺሻ ዕቃና 8 ወጣቶች
ናሽናል ሆቴል፦ 16 የሺሻ ዕቃ እና 67 ወጣቶች
ሞሲሳ ሆቴል፦ 7 የሺሻ ዕቃዎች
በቦሌ ክፍለ ከተማ
5.ቀነኒሳ ሆቴል፦ 35 የሺሻ ዕቃዎች
6.ዘባንክ ላውንጅ፦ 28 የሺሻ ዕቃዎች
የካ ክፍለ ከተማ
ቤልቪው ሆቴል፦ 86 የሺሻ ዕቃ እና 54 ሰው
በአጠቃላይ በሦስት ክፍለ ከተማ 7 ቤቶች ታሽገዋል፤ 281 የሺሻ ዕቃዎች እና 330 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ 200 ወጣቶች በምክር እንዲለቀቁ ተደርጓል።
130 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው በሕግ መታየት መጀመሩን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።
በተከናወነው ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሰላም እና ፀጥታ፣ የደንብ ማስከበር እንደተሳተፉበት ተገልጿል።
EBC
Leave a comment

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies