አበበ ፈንታው / የማህበራዊ ሳይንስ ፣ ላብራቶሪ ቴክኒሻል / የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት የማገገሚ ማዕከል አሰልጣኝ

“እፆችን መጠቀም የጀመርኩት በ13  አመቴ አካባቢ ነበር፡፡ የተለያዩ እፆችን በመጠቀም ለ16 አመታት ሱሰኛ የነበርኩኝ ሲሆን በእዚህም የተነሳ  ለተለያዩ  ችግሮች ፤ ስነ-ልቦናዊ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጥሁ ነበርኩ ፡፡

ነገር ግን እነዚያ አስቸጋሪ ጊዜያት አልፈው ዛሬ ከሱስ ህመም በማገገም የተሻለ ሕይወት እየኖርኩ ነው ፡፡ እውነተኛ ሕይወት እና መዝናናት በእፆች መጠቀም እንደማይገኙ ተረድቻለሁ ፡፡

ለዚህም በመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት የማገገሚያ ማእከል አገልግሎት የአቻ ድጋፍ  ሰጪ አገልግሎት እና ለማገገሜ በሚረዱሩኝ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች እንዲሁም ግንዛቤ ፈጣሪ ዝግጅቶች ውስጥ በማለፊና በመታገዜ እንድበረታ ትልቅ አስተዋጽዖ አድርጎልኛል፡፡

ለሕይወቴ መሻሻል እንቅፋት የሆኑትን የአደንዛዥ አስተሳሰቦች በመረዳቴ እና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣቴ እና እፆቹኑ መጠቀም ለማቆም ቁርጠኛ በመሆኔ ከሚሰጠኝ እገዛ ጋር የተሸለ ውጤት ለማየት እንድችል አድርጎኛል፡፡

ሆኖም ግን እኔም እንደማንኛውም ሱሰኛ ካቆምኩ ቡሃላ በጉዞ ውስጥ አንድ አካል የሆነው ምልሰተ ሱስ  አጋጥሞኝ የነበረ ሲሆን ዛሬ ራሴን በማሻሻል በእዚህም ጉዞ ውስጥ ለ11 አመታት እያሳለፍኩ ነው ፡፡

በዚህም በመቋሚያ የማህረሰብ ልማት ድርጅት የማገገሚያ ፍልስፍና ሌሎች ለእኔ ያደረጉልኝን “መቋሚያዊ” ድጋፍ እኔም ለሌሎች “መቋሚያ” በመሆን ድጋፍ ሆኘ በማገሚያ ማእከል ውስጥ አሰልጣኝ ሆኘ እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡

ለእዚህም የድል ሕይወት በመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅትን የተደረገልኝ አገልግሎት ድጋፍ በመሆኑ አመሰግናለሁ!!

ዛሬም የመቋሚያ የአቻ ድጋፍ ቡድን ተጠቃሚ በመሆኔ ደስታ ይሰማኛል”

 

 አበበ ፈንታው

/ የማህበራዊ ሳይንስ ፣ ላብራቶሪ ቴክኒሻል /የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት የማገገሚ ማዕከል አሰልጣኝ

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies