TRAINING OF TRAINERS FOR ETHIOPIA ON THE UNIVERSAL CURRICULUM PREVENTION /TREATMENT FOR SUBSTANCE USE DISORDERS

ሱስ በሽታ ነው!

ማህበረሰብም እንደ ግለሰብ ይታመማል። ግለሰብ በአካሉ ሲታመም በተክለ ሰውነቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚከሰትበት ሁሉ ማህበረሰብም ሲታመም ማህበራዊ ቁመናው ላይ እክል ያጋጥመዋል ። በዚህም ሀገር ትታመማለች።

የግለሰብ ስነልቦናዊና አካላዊ እና መንፈሳዊ ህመም ወደ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህመም ሊቀየር እንደሚችል ጥናቶች እንደሚጠቁሙን ሁሉ የማህበረሰብ ሳይንስ ሊቃውንት የከፋ ችግር ሊያመጡ ከሚችሉ ክስተቶች ፤ ህመሞች/በሽታዎች መካከል ውስጥ የሱሰኝነት በሽታን ከቀዳሚዎቹ ተርታ ያስቀምጡታል ።

የሱስ በሽታ የሱሰኛውን አዕምሮ ስለሚቆጣጠረውና የአዕምሮ ተፈጥሯዊ ስርአቱን ስለሚያዛባው ግለሰቡ በእፁና እፁ በሚዘውረው የተዛባ አዕምሯዊ ስርአት ስር በቁጥጥር ስር ይውላል (በባርነት ስር ይወድቃል) ።
በዚህም እፆችን ወይም አልኮል መጠጦችን ወሳጁ ግለሰብ ከተጠቃሚነት ወደ ሱሰኝነት ከተሸጋገረ የጉዳቱም መጠን እየጨመረ በውስጣዊ አካሉና ስነልቦናው ላይ ከሚደርሰው እክል ባለፈ እስከ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ መተረማመስ ድረስ ይደርሳል በዚህም የሀገር መሰረት የሆነው ቤተሰብ ላይ የከፋ ችግር ይደርሳል የዚህም ድምር ውጤት ሀገርን የሚያተረማምስ ሆኖ ሳለ የሚገባውን ያህል ለመፍትሄው ትኩረት በበቂ መጠን ሳይሰጠው ችላ የተባለ ህመም ሆኖ ቆይቷል። እንላለን።
ይህ በሽታ የግለሰብና የቤተሰብ ሰላም ፀር ከመሆኑ አልፎ ተርፎ ለሀገርም ሰላምና ኢኮኖሚ መዎዠቅ፣ ለፖለቲካ መተረማመስ ምክንያት መሆን የሚያስችል ጉዳዮችን የሚቀሰቅስ ስለመሆኑም ጥናቶች ይጠቁማሉ ።

ሱሰኝነት የሚድን እና የምንከላከለው በሽታ ነው!

ታዲያ ይህንን ህመም እንደ ሌሎቹ ህመሞች ሁሉ በህክምናና መልሶ በማቋቋሙ ዙሪያ እንዲሁም በቅድመ መከላከል እና ትውልድን ጠባቂ ከልካይ ህጎችን በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ መቆጣጠር የሚያስችል መሰረት መመስረት ሀገርን ከከፋ ጉዳት ትውልድን ለበለጠ ልማት ማነሳሳት የሚያስችል ይሆናል ።

እስከዛሬ የችግሩ ግዝፈትና ጥልቀት እንዲሁም ስርጭት እያመጣ የነበረው መጠነ ሰፊ ጉዳት ችግሩን ለመቅረፍና ለመቆጣጠረሰ ከሄድንበት ርቀት ጋር ሲወዳደር እጅግ በጣም የሰማይና የምድርን ያህል የተራራቀ ነው ።

በመሆኑም በዚህም መስክ ያለውን ሀገር አቀፍ በዘርፋ ያለውን ከፍተኛ የሙያተኛ እጥረትና ችግሩን ለመቋቋም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ሀገራዊ ካለም አህጉራዊ ደረጃ ለማድረስ መቋሚያ ላለፋት አስር አመታት ሲሰራበት የነበረ መሆኑ ይታወቃል ።በዚህም ጅምር የሆነ የመንግስትን ትኩረት የመስጠት ደረጃ ስላየን እናመሰግናለን ።ሆኖም ግና ትኩረቱ ሊጠናከር እንደሚገባ ወላጃቸውን ወይም አሳዳጊያቸውን በሱሰኝነት በሽታ አተው በሚሰቃዩ ህፃናትና ልጆቻቸውን በሱስ በሽታ የተነጠቁ ወላጅና አሳዳጊ እናቶች ስም እንለምናለን ። ሀገር ማለት ሰው ነው!
*

መቋሚያ እስከዛሬ ሲሰራው ከነበረው በተሻለና በተቀናጀ መልኩ ለመስራት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋረሰ በመሆን አለም አቀፍ የ70 አመት እውቅና ካለው እና የአህጉራት ህብረትና (AU,US,EU…) UN ጋር የሚሰራው ከColombo plan Drug Advisory program ጋር በመተባበር የሌሎች ሀገራትን ልምድ በመቅሰም እና በተለያዩ ሀገራት ስልጠናዎችን በአካል በመገኘት በመውሰድ ዘመኑ የደረሰበትን እውቀት በመታጠቅ አገራችንን እና አህጉራችንን አፍሪካ ከመዘዙ ለመታደግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የአለፈውን ሁለት አመት እየሰራን እንገኛለን ።
*

ይህ በእንዲህ እንዳለ በባለፈው ሳምንት ማለትም 10-16/03/2011ዓ.ም ሚኒስቴር መስራቤቶች የክልል የጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል ተጠሪዎች ከዘርፋ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ባለሙያዎች በጥቅሉ 31 ሰልጣኞች ” የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነትን እና የሱሰኝነት ህመምን ለመከላከል እና የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የመጀመሪያ ደረጃ አለም አቀፍ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ”
TRAINING OF TRAINERS FOR ETHIOPIA ON THE UNIVERSAL CURRICULUM PREVENTION /TREATMENT FOR SUBSTANCE USE DISORDERS (UPC 1,UTC 1)
ይህ ስልጠና ሲሰጥ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በስልጠናውም መቋሚያ አዘጋጅና አስተባባሪ በመሆን የሰመረ የስልጠና ጊዜ እንዲሆን አስተዋፅዖዎን አድርጋለች። በስልጠናውም 5 የመቋሚያ ሰራተኞች የአሰልጣኞች አሰልጣኝ በመሆን ሰልጥነው የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብለዎል።
*
ይህ ስልጠና ለሀገራችን ያለው ፋይዳ በዘርፋ ገና በጅምር ያለውን የቅድመ መከላከል እና የማገገሚያ ማእከላት ስራ ባለሙያዎችን በብቃት በማሰልጠን በየክልሉና በየደረጃው ለመፍትሄው እየወጠንን ያለውን ስራ በበለጠ እንዲጠናከር በማድረግ በመፍትሄው ተስፋ ያዘለ እንቅስቃሴ እንዲኖር አስተዎፅዖው ከፍ ያለ ይሆናል ከዚሁ እኩል በጤናው ሴክተር ለሱስ በሽታ ይበልጥ ትኩረት እንዲደረግ የሚያስችል የመቋሚያ አጋዥ ሰራዊት ፤ደጀን በመሆኑ ጥሩና የተሻለ አጋጣሚም እንደሚፈጥር እናምናለን።

ሱስ የምንከላከለውና የሚድን በሽታ ነው !

ሀገራችን ከዜጎቾ አንንጎልና አዕምሮ የበለጠ ሀብት የላትም!

ስለዚህ አስገራሚና አስደናቂ ስልጠና ጤና ሚኒስቴርን (MoH) እና Colombo plan DAP ከልብ በመነጨ ምስጋና ልናመሰግን እንወዳለን

Thank you a lot MoH and Colombo plan DAP

Leave a comment

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies