100% Smoke Free Addis (SF)

Mekoamia in partnership with Campaign for Tobacco-Free Kids (CTFK) and Tobacco-Free Kids Action Fund (TFKAF), supports the implementation of 100% Smoke-Free (SF) provisions contained under the tobacco control proclamation by bars and restaurants, nightclubs, and lounges in Arada Sub-city.

The project kicked off on April 1, 2021 aims to accomplish:                                                                                                    1.

  1. Sensitize Addis Ababa Food, Medicine and Health Care Administration and Control Authority (AAFMHACA) and Arada sub-city health offices on SF implementation in bars and restaurants, nightclubs, and lounges.
  2. Provide capacity building and technical assistance for 100% SF provisions enforcement by bars, restaurants, coffee houses, and nightclubs in the Arada sub-city.

ከትንባሆ ጭስ የፀዳች አዲስ አበባ

መቆዋሚያ ከ ከካምፔይን ፎር ቶባኮ ፍሪ ኪድስ እና ቶባኮ ፍሪ ኪድስ አክሽን ፈንድ ጋር በመተባበር የትንባሆ ቁጥጥር አዋጅ ውስጥ የተካተተውን 100% ከትንባሆ ጭስ የፀዳች አዲስ አበባ የመፍጠር ሃሳብ በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ባሮች ሬስቶራንቶችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል::

ይህ ፕሮጀክት የሚክተሉትን ተግባራት ያከናውናል

  1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣የመድሀኒት የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣንን እንዲሁም በአራዳ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኙ የጤና ቢሮዎችን በማነሳሳት በባሮች ሬስቶራንቶችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ውስጥ 100% ከትንባሆ ጭስ የፀዳች አዲስ አበባ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል::
  2. በአራዳ ክፍለ ከተማ በቡና ቤቶች፣ በሬስቶራንቶች፣ እና በምሽት ጭፈራ ቤቶች  100% ከትንባሆ ጭስ የፀዳች አዲስ አበባን ድንጋጌ ተፈጻሚ እንዲሆን የአቅም ግንባታ እና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል::

የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር – 1112/2011
የትምባሆ ምርትን ማጨስ እና መጠቀም ስለሚከለከልበት ቦታ

አንቀፅ 1/ ማንኛውም ሰው ከበር መልስ ባለ ለህዝብ ክፍት በሆነ ማንኛውም ቦታ ፣ ከበር መልስ ባለ ማንኛውም የሥራ ቦታ ፣ በሁሉም የህዝብ መጓጓዣ እና በጋራ መኖሪያ ቤት በማንኛውም የጋራ መገልገያ ቦታ ላይ ማጨስ ወይም ትንባሆን መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

አንቀፅ 2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ- አንቀጽ (1) መሰረት ማጨስ ወይም ትንባሆን መጠቀም በተከለከለባቸው ከበር መልስ ባሉ ለህዝብ ክፍት በሆኑ ቦታዎች እና የሥራ ቦታዎች በአሥር ሜትር ዙሪያ ውስጥ ባለ መግቢያ በር ፣ መስኮት ወይም አየር ወደ ውስጥ ሊያስገባ በሚችል ሌላ ቦታ ውስጥበማጨስ የተከለከለ ነው፡፡

አንቀፅ 3/ የዚህ አንቀጽ ንዑጽ-አንቀጽ (2) ቢኖርም በማንኛውም የጤና ተቋም ፣ የመንግሥት ተቋም ፣ በዋናነት ለህጻናት እና እድሜው ከ21 አመት በታች ለሆነ ሰው አግልግሎት የሚውል ትምህርት ቤትን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ማንኛውም ሌላ ፤ በወጣት ማዕከል ፣ በመዝናኛ ፓርክ እና ሌላ በአስፈጻሚ አካሉ ወይም በክልል ጤና ተቆጣጣሪው በሚወስን ከበር ውጭ ባለ ሌላ ቦታ እና ቅጥር ግቢ ውስጥ ማጨስ ወይም ትምባሆ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

ከትንባሆ ምርት ነጻ የማድረግ ኃላፊነት

አንቀፅ 1/ የትምባሆ ምርት ማጨስ ፣ መጠቀም ወይም መሸጥ የተከለከለባቸው ቦታዎች ወይም ማጓጓዣ ባለንብረት ወይም ለማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው ሰው በእነዚህ ቦታዎች የትምባሆ ምርት እንዳይጨስ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል ፣ እንዳይሸጥ እና የሲጃራ መተርኮሻ ወይም ሌላ የትምባሆ ምርትን ለመጠቀም የሚያገለግል ማንኛውም ዕቃ እንዳይቀመጥ መከልከል አለበት፡፡

አንቀፅ 2/ ለህዝብ ክፍት የሆነ ቦታ ወይም ማጓጓዣ ባለንብረት ወይም ሌላ ኃላፊነት ያለበት ሰው ወይም የሥራ ቦታን በተመለከተ አሰሪ ወይም ሌላ አግባብ ያለው ሰው በጉልህ የሚታይ ትምባሆ ማጨስ ወይም መጠቀም የተከለከለ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከነባለቀለም ምልክቱ የመለጠፍ ግዴታ አለበት፡፡

የአዲስ አበባ ም/መ/ጤ/ክ/አሰ/ቁ
አስተዳደራዊ ቅጣት

  • ማስጠንቀቂያ
  • ፍቃድ ማገድና መሰረዝ
  • ምርትን መያዝ ፣ ማገድ ፣ መውረስ ፣ እና ማስወገድ
  • በደንቡ መሰረት የገንዘብ ቅጣት

የወንጀል ቀቅጣት

  • ትምባሆ መሸጥ በተከለከለ ቦታ መሸጥ ከ 6 ወር በማይበልጥ ቀላ እስራት ወይም ከ5000 በማይልጥ መቀጮ (ን .20)
  • ትምባሆ ማጨስ / መጠቀም በተከለከለ ቦታ ማጨስ ከ1000 ብር በማይልጥ መቀጮ (ን.20)
  • ትምባሆ ማጨስ የሚከለክል ምልክት ያለጠፈ ወይም ሲጨስ እርምጃ ያልወሰደ ከ3 ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከብር 1000- 10000 (ን.22)

    ከትምባሆ ነፃ ተቋም ማለት ተቋሙ ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መስፈርቶች አሟልቶ ሲገኝ ነዉ፡፡

  • የተከለለ የማጨሻ ስፍራ የሌለው
  • የሚያጨሱ ሰዎች ቦታው ላይ ካልታዩ
  • ማጨስ የሚከለክሉ ስቲከሮች ከተለጠፉ
  • መተርኮሻ፣ ላይተር የመሳሰሉት እቃዎች ከሌሉ
  • የሲጋራ ቁራጭ ቦታዉ ላይ ካልታየ
  • የሲጋራ ጭስ ሽታ ከሌለ

በአንድ ጥቅል ሲጋራ /ትምባሆ / ውስጥ የሚገኙ የንጥረ ነገሮች ብዛትና ጉዳታቸው

  • 7,357 በላይ ንጥረ ነገሮች አሉ
  • 250ዎቹ ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጮች ሲሆኑ 70ዎቹ ደግሞ ለካንሰር አጋላጮች /carcinogenic activity/

ምንጭ፡ compound interest 2015
በትምባሆ ተጠቀሚዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ጉዳቶች

  • የጉሮሮ ካንሰር
  • የልብ እና የደም ስር በሽታዎች
  • የሳንባ እና የጨጓራ ካንሰር
  • የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ
  • የቆዳ መጨማተር
  • የድድ መቁስል
  • ስንፈተ ወሲብ
  • የጀርባ ህመም
  • ቋሚ ሳልና ጉንፋን
  • የስነ ተዋልዶ ችግር፡
  • በሴቶች ፡ የፅንስ መጨንገፍ ፣ ካለ ጊዜው መውለድ ፣ ክብደቱ አነስተኛ ልጅ የመውለድ ጉዳት ያደርሳል፡፡
  • በወንዶች፡ የስፐርም ሴል መቀነስ እና ስንፈተ ወሲብ ያስከትላል፡፡

የተለያዩ ቀላልና ከባድ የጤና መዛባቶችን እንዲሁም እስከ ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ይታወቃል
ጥናቶች እንደሚጠቁሙን የትንባሆ ተጠቃሚዋች የግል ጤንነታቸው ከመጉዳት ባሻገር በዙሪያቸው መኖር ተፈጥሯዊ ምብቴ ነው!!

 

addis smoke free

Meqoamia Community Development Organization (MCDO) is a non-profit civil society organization that played a critical role in establishing treatment, prevention, and recovery coaching especially, for those with substance abuse issues or Addiction. Moreover, the organization has been giving psychosocial support to individuals in need. 

© All Rights Reserved. Privacy Policy | Powered by Geez Web Technologies