University Based Anti- Addiction Community Movement -2026/2018
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው የ UBAACM ንቅናቄ፦ “ጤናማ አንጎል = የትምህርት ጥራት = ዘላቂ ስኬት”
በመጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም (March 31, 2026) በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እጅግ ድንቅ እና ታሪካዊ የሆነ የምክክርና የስልጠና መድረክ አካሂደናል። የ ‘ዩኒቨርስቲን መሰረት ያደረገ የጸረ-ሱስ ማህበረሰብ ንቅናቄ’ (UBAACM – 2018/2026) በይፋ ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ በመድረኩም በርካታ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

“መቋሚያ” – የሱስ ሳይንስ ስልጠና
የዕለቱ ዋና አሰልጣኝ የነበሩት የ MCDO ዋና ስራ አስኪያጅ እና የ DDR ተሟጋች ኤልያስ ካልአዩ ነበሩ። ኤልያስ በቅርቡ ለ 4ኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በበቃውና በሰፊው ተቀባይነትን ባገኘው “መቋሚያ – የሱስ ሳይንስ” መጽሐፋቸው ላይ በመመስረት ጥልቀት ያለው ስልጠና ሰጥተዋል።
ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች፡-

- ጤናማ አንጎል (Healthy Mind): የሱስ ሳይንሳዊ ምንነትና በአንጎል ላይ የሚያደርሰው ጉዳት።
- የትምህርት ጥራት (Education Quality): ከአደንዛዥ ዕፅ የጸዳ ተማሪ ለትምህርት ጥራት ያለው ሚና።
- ዘላቂ ስኬት (Sustainable Success): ሱስን በመከላከል እንዴት የተሳካ የህይወት ጉዞ መጓዝ እንደሚቻል።
የንቅናቄው ዓላማ
ይህ በ MCDO አስተባባሪነት የተጀመረው የ 2018/2026 ዓ.ም የ UBAACM ንቅናቄ፣ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ የአደገኛ ዕፅ ተጠቃሚነትን ለመከላከል፣ ግንዛቤን ለማሳደግ እና ክህሎትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት ያለመ ነው።
በዕለቱ የነበረው የተማሪዎች ተሳትፎ እና ለለውጥ ያላቸው ዝግጁነት ለንቅናቄው ትልቅ ተስፋን የሰጠ ነበር። “ጤናማ አንጎል = የትምህርት ጥራት = ዘላቂ ስኬት” የሚለው መሪ ቃልም በሁሉም ዘንድ የጋራ መግባባት ተፈጥሮበታል።
በመጨረሻም፣ ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ድጋፍ ላደረጉት ለሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ለተሳታፊ ተማሪዎች በሙሉ በ MCDO ስም ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን።
MCDO – መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት March 31, 2026
UBAACM Movement Launched at Hawassa University: “Healthy Mind = Education Quality = Sustainable Success”
On March 31, 2026, we held an extraordinary and historic consultative and training forum at Hawassa University. The ‘University-Based Anti-Addiction Community Movement’ (UBAACM – 2018/2026) has officially been launched, with a significant number of students and members of the university community in attendance.
“Meqoamia” – The Science of Addiction Training

The lead trainer for the event was Elias Kalayu, Executive Director of MCDO , DDR Advocate and a Author, Elias provided in-depth training based on his widely acclaimed book, “Meqoamia – The Science of Addiction” (4th Edition).
The training focused on key pillars:
- Healthy Mind: The scientific nature of addiction and its impact on the brain.
- Education Quality: The vital role of drug-free students in maintaining high educational standards.
- Sustainable Success: How to navigate a successful life journey by preventing addiction.
Objectives of the Movement

Initiated and coordinated by MCDO, the 2018/2026 UBAACM movement aims to prevent drug abuse among university students, raise awareness, and build capacity through skill-based interventions.
The level of student participation and their readiness for change during the event was highly encouraging for the movement’s future. The motto “Healthy Mind = Education Quality = Sustainable Success” was embraced by all participants as a shared vision.
Finally, on behalf of MCDO, we would like to express our deepest gratitude to the Hawassa University administration and all participating students for making this program a success.
MCDO – Meqoamia Community Development Organization March 31, 2026

